Friday, January 13, 2012

የጥየቄ ፫ መልስ


እግዚአብሔር ፍጥረታትን በ፮ ቀን እንደጨረሰ በዘፍጥረት ፩ ተጠቅሶአል። አንድ ቀን የምንለው ፀሐይ ፡ወጥታ፡ ገብታ መልሳ እስክትወጣ ያለውን ፳፬ ሰዓት ነው። ፀሐይ ግን የተፈጠረች በአራተኛው ቀን ረቡዕ ነው። ቁ ፲፬። ታዲያ ከዚያ በፊት የነበሩት ፫ ቀናት (ከእሑድ- ማክሰኞ) በምን ተቆጠሩ?
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጥያቄዎች አብረን ማየት አለብን። በዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመርያ ክፍለ-ንባብ የተጻፈን ነገር በማስተዋል ብንመረምር ልዩ የሆነ ውጤት እናገኛለን፡፡
«በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡ ምድርም ባዶ ነበረች፡፡ አንዳችም አልነበረባትም፡፡ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር፡፡...» ዘፍ፣፩-፪
·        ምድር ለምን ያህል ጊዜ ባዶ ሆና ኖረች?
·        ጨለማስ በጥልቁ ላይ ስንት  ዘመን  ኖረ?

እነዚህን ጥያቄዎች በማከተል እስከ ቁጥርድረስ «ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አንድ ቀን» እስካለው እያነሳን መጠየቅ እንችላለን፡፡
«እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።» ዘፍ ፩፡፭።
·        «ማታ» ማለት ምን ማለት ነው? «ጥዋት» ማለትስ? አሁን በምናውቀው ክስተት ማታ የሚባለው ፀሐይ ስትጠልቅ ሲሆን ጥዋት የሚባለው ግን ፀሐይ ስትወጣ ነው። በመጀመሪያዎቹ ፫ የፍጥረት ቀናት ግን ፀሐይ አልተፈጠረችም።
·        «ማታም ሆነ» ካለ በኋላ «ጥዋትም ሆነ» ይላል፡፡ ከሆነ በኋላ ጥዋት እስኪሆን ድረስ ስንት «ሰዓት» ወይም  «ዘመን» አለፈ? ምናልባት  አንድ ቀን   እስከተባለ ድረስ በቁጥር አንድና ሁለት ያሉት ድርጊቶች በሰዓታት ጊዜ የተከናወኑ ናቸው ብለን መልስ እንሰጥ ይሆናል፡፡
·        ለመሆኑ አንድ ቀን የተባለው ምን ያህል ጊዜ አለው? ዛሬ አንድ ቀን የምንለው 24 ሰዓ ያሉት ጊዜ የሚታወቀው /የሚሰፈረው/ በፀሐይ መውጣትና መግባት ወይም መሬት በራሷ ዛቢያ አንድ ዙር ስትዞር እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ አሁንም በመጀመርያው ቀን ፀሐይ ገና አልተፈጠረችም፡፡ የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት «ቀን» እየተባሉ ከመጠቀሳቸው በቀር በምን እንደተለኩ / ስንት ጊዜ እንደሆኑ በግልጽ የተጻፈ ነገር የለም፡፡ ይህ ጊዜ አሁን በምንጠቀምባቸው የጊዜ መለኪያዎች ጥቂት ሴኮንዶች ወይም ሚሊዮን ዓመ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ነው ተብሎ ተለይቶ የተቀመጠ ነገር የለም፡፡
ዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያልሆነ ነገር ለምን አስቀመጠ? ሰዎች አንብበው ለመረዳት እንዲቸገሩ? ወይስ እንዲመራመሩ?
የመጽሐፍ-ቅዱስ የአጻጻፍ ዘይቤና የሃሳብ ምጥቀቱ እጅግ የሚያስደንቅ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አንድ ፀሐፊ የሚከተለውን አስፍርዋል፡፡
«The genius of the Bible primarily lies in the fact that it is written in a concise and plain language which can be understood in any era, by any nation, by all kinds of people, regardless of their level of intellectual development.
/«God exists» ... Joseph Davy dov ገጽ 24/
«የመጽሐፍ ቅዱስ በሳልነት ከሁሉም በላይ የሚወቅበት እውነታ በተመጠነ እና ግልጽ በሆነ ቋንቋ መጻፉ ሲሆን በየትኛውም ዘመን፣ በየትኛውም ቦታ፣ በየትኛውም የዕውቀት ደረጃ ላለ ሁሉም ሰው ሊረዳ የሚችል ነው፡፡»
    መጽሐፍ-ቅዱስ ከሰዎች የኑሮ ልማድ ጋር በየጊዜው መሻሻል የማያስፈልገው አንድ ጊዜ የተጻፈና ሁልጊዜ እየተነበበ ሕይወትን የሚመራ ልዩ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በጥያቄ ያነሳነው የመጀመርያው ክፍለ-ንባብ እንደየአካባቢዎቹ የዕውቀትና የመረዳት ደረጃ ሊስማማ ይችላል፡፡ ብዙም ላልተማረ የኔብጤ መሃይም ሆነ በጥልቀት ለሚመራመር ሳይንቲስት ለሁለቱም በየራሳቸው በሚረዳ መልኩ ተጽፎአል፡፡ ሁለቱም ሰዎች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ለሰዎች ነው፡፡
v እንደመጀመርያው የኔቢጤ ሰው ብናይ... ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አንድ ቀን በማለቱ ይህ አንድ ቀን አሁን በምናውቃቸው 24 ሰዓቶች አካሄድ የተነገረ ነው በማለት ሊረዳው ይችላል፡፡ ይህ እንግዲህ በጥሬ ቃሉ ቀጥተኛ ተጠቃሽነት ሲሆን ፀሐይ ሳትፈጠር እንዴት ቀን ተባለ? ላልነውም በመተርጉማን መብራራት ያስፈልገዋልና መምህራኑ «ፀሐይ 4ኛው ቀን ተፈጥራ ወደ ኋላ ሦስት ቀን አብርለች» ብለው ያስርቁለታ ል፡፡ ከረቡዕ በፊት ያሉት ቀኖች እንደኋለኞች መሆናቸውን ፍጥረ 6 ቀን እንደተፈጠሩ በሌላ ቦታ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ዘጸ፡፲፩፡፡
v እንደሁለተኛው ሳይንቲስት ሰው ብናይ ደግሞ ቀደም ብለን የጠየቅናቸውን በማንሳት በጥልቀት ስንመረምር የመጀመርያው ክፍለ-ንባብ ይሄ ነው ተብሎ ተመጥኖ የተቀመጠ ጊዜን ስላልያዘ እግዚአብሔር እንድንመራመርበት የተወው ክፍት የጊዜ ሥፍራ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ለዚህም አሁንም በመጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን በኛ ሺህ ዓመት መሆኑን የሚናገር ማስረጃ እናገኛለን፡፡መዝ ፹፱/፺፤፬ ፡፡ ሺህ ሲባልም በትክክል አንድ ሺህ ሳይሆን ብዛትን ወይም ፍጹም ሊቆጠር የማይቻል ማለት መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ የአነጋገር ዘይቤ ወቀ ነው፡፡ 


………(ይቀጥላል)

No comments:

Post a Comment

Give comments, አስተያየትዎን ይስጡ።