ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ዮሐ ፩፡ ፩-፫።
ሁሉ በእርሱ እንዲያምኑ፡- ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ። ዮሐ ፩፡ ፯።
ስለርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈ፡- ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። ሉዋ ፳፬፡፳፯።
ሁሉ ከአባቱ ዘንድ የተሰጠው፡- ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ማቴ ፲፩፡፳፯።
በፈጣሪነቱ - ሁሉ በእርሱ፡ የተፈጠረ፡- የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።
በአዳኝነቱ - ሁሉ ለእርሱ የተፈጠረ፡- የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ቆላ ፩፡፲፮፡፡
ከሁሉ በፊት የነበረ፡ ሁሉ በእርሱ የተጋጠመ፡-
እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል። |
እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው። ቆላ ፩፡፲፰። |
|
....ይህን በሐዋርያት የተገለጠውን እውነት ስለመሰከርህ ደስ ብሎኛል። ቃሉም የሚለው «የሉቃስ ወንጌል 12፥8 እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል» ያለውን ዋጋ ያለጥርጥር ትቀበላለህና።
ReplyDelete