እግዚአብሔር የመረጠው ጾም
እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? ኢሳ ፶፰፡ ፮-፯።
እግዚአብሔር የሚለመንበት መንገድ
በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።
ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን እርሱም ተለመነን። ዕዝ ፰፡፳፩-፳፫
ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበት መንገድ
አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።
ኢዩ ፪፡፲፪
ከልመና (ከጸሎት) ጋር የሆነ ጾም
ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ ዳዊትም ጾመ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ። ፪ሳሙ ፲፪፣፲፮
በመዋረድ የሆነ ጾም
አክዓብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ ገላውን ማቅ አለበሰ፥ ጾመም፥ በማቅ ላይም ተኛ፥ ቅስስ ብሎም ሄደ። ፩ነገ ፳፡፳፯።